ዜና ዜና

የኤክስፖርት ምርትና ግብይትን በማሳደግ በአገሪቱ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲሰፍን ይደረጋል- ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

በ5ተኛዉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ና የፌደረሽን ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ  ስበሰባ ላይ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ንግግር አድርገዋል፡፡

የኤክስፖርት አቅምን በማሳደግ እና በአገር ዉስጥ የቁጠባ ባህልን በማጠናከር የዉጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት እንደሚሰራ ለሁለቱ ምክር ቤት አባላት ገልፀዋል

በ2010 ዓ.ም. በአገሪቱ  የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲሰፍን  የኤክስፖርት  ምርትና ግብይትን መጠን እና ጥራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እንደገለፁት ለኤክስፖርት ገቢ 80% አስተዋጽኦ ለሚያበረክቱት ቡና ፤ሰሊጥ ጥራጥሬ፤ቅመማቅመም ፤አበባባ የቁም እንሰሳት መጠንና ጥራት  ማሳደግ ትኩረት  ይሰጠዋል ብለዋል፡፡

በማእድናትና ጌጣጌጥ ዘርፍ የተሰማሩ እና የኢንዱስትሪ ፓርክ  ምርት ውጤቶችም በፍጥነት ወደ ኤክስፖርት ገበያው እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

በተያዘው በጀት አመት በትልልቅ ግብር ከፋዮች ላይ ትኩረት ከማድረግ ባለፈ በኮንስትራክሽን ፤ በማምረቻዉ ዘርፎችና በሌሎች  ተሰማርተዉ ከግብር እፎይታ በኋላ ወደ ግብር መስመሩ ያልገቡ አካለት ላይ በትኩረት  እንደሚስራ አብራርተዋል፡፡

 የግብር አሰባሰቡን በማዘን ፤የታክስ ኦድት አለም አቀፍ ተሞክሮችን በመውስድ በበጅት አመቱ ኢኮኖሚውን የሚመነጨውን ለመሰብሰብ ይሰራል ብለዋል፡፡

በተያያዘም በ2009 ዓም የዋጋ ግሽበቱ ከነጠላ አሀዥ በላይ እንዳይሆን መንግስት የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑን ጠቁመዋል፡፡

መንግሰት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ፤የዋጋ ማረጋጊያ የእህል ክምችት በመያዝ ፤የፊሲካል የዉጭ ምንዛሬ ተመን ፖሊሲዎችን በመከተል የዋጋ ንረቱን መቆጣጠር መቻሉን አብራርተዋል፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 30/01/2010