ዜና ዜና

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ችግር መረጋጋቱን ክቡር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ገለፁ

በትናትናው እለት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠው ግጭት ምክንያት ከጅግጅጋ እና አወዳይ ከተሞች 600 ያህል ነዋሪዎች ወደ ሀረር ከተማ ሸሽተው መግባታቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጅ በዛሬው እለት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ጽ/ቤት ሀላፊ ሚንስተር ዶክተር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ እንደገለጹት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ከሁለቱም ክልልሎች አመራሮች ጋር በመሆን ግጭቱን መቆጣጠር ችለዋል፡፡ እንደሚንስትሩ ገለጻ የሁለቱም ክልሎች ተዋላጆቹ ወደ እየመጡበት ከተማ የመመለስ ስራም ተጀምሯል፡፡

የሁለቱ ክልል ህዝቦች ለዘመናት በሰላም ተከባብረውና ተቻችለው አብረው የኖሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር የመፍታት አቅም ያለው የሁለቱ ክልሎች ህዝብና አመራሮች በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚንስትሩአሳስበዋል፡፡
መስከረም3/2010 ዓ.ም