ዜና ዜና

በደቡብ ክልል በበቆሎ ላይ የተከሰተውን መጤ ተምች ለመከላከል አርሶ አደሮች በህብረት እየሰሩ ነው

በደቡብ ክልል በበቆሎ ሰብል ላይ የተከሰተውን የአሜሪካ መጤ ተምች ለመከላከል አርሶአደሮቹ በህብረት ያደረጉት ጥረት ተምቹን ለመቆጣጠር እያገዛቸው ነው፡፡

ሆኖም በበልግ ሰብል ላይ ለምርት መቀነስ ምክንያት የሆነው ተምቹ ወደመኸር ሰብሎች ላይ እንዳይዛመት ስጋት አለ፡፡

ይህንን ከወዲሁ ለመቆጣጠር የቅድመ መከላከል ስራው እየተካሄደ ነው፡፡
ኢቢሲ፣ ነሀሴ 17/2009