ዜና ዜና

በሁለቱ ክልሎች የወሰን ማካለል ሥራ እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች በተደረሰው ስምምነት መሠረት የወሰን ማካለል ሥራ መጀመሩን የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ዛሬ ማምሻውን አስታወቁ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ እንደገለጹት በድንበር ማካለሉ ወቅት አንዳንድ ፈቃደኝነት ያላሳዩ ሰዎች በመኖራቸው ምክንያት ኮሚቴው ለጊዜው ሥራውን አቋርጦ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ነገሪ አያይዘውም ይህንኑ አለመግባባት አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ጦርነት እንዳለ በማስመሰል ማሰራጨታቸውን ጠቅሰው ፤ ያልተጣራ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ ስላልሆነ መረጃን ከተገቢው አካል አጣርቶ መውሰድ አስፈላጊ ነው በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ነሀሴ 4/2009