ዜና ዜና

ኢትዮጵያ የቻይና፣ ኮሪያና ህንድ የአልባሳት አምራቾችን እየሳበች መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ የቻይና ኮሪያና ህንድ የአልባሳት አምራቾችን እየሳበች መሆኑ ተገለፀ፡፡

ኤስያ ኒኬይ የተባለው ደረ ገፅ እንደዘገበው ወጣት የሰራተኛ ኃይል መኖሩና ለኢንቨስትመንት አምች ሆኔታዎች እተፈጠሩ መምጣታቸው የኢስያ አለባሳት አምራች ኩባንያዎችን ለመሳብ አስችሏል፡፡

በተለይም የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር መገንባት ለወጪ ምርት ገበያው አምችነት ሲባል በጨርቃጨርቅና አልባሳት ላይ የተሰማሩት ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ እያስቻለ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

ለአብነት በቦሌ ለሚ የኢንዱስተሪ ፓርክ የተሰማሩትን የቻይና፣የታይዋንና የደቡብ ኮሪያ በጨርቃጨርቅ፣በአልባሳትና በቆዳ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች በአንድ ማዕከል አምርተው ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የያዙት ጥረት ትልቅ ተሰፋ ሰጪ ጅምር መሆኑም ዘገባው ያስረዳል፡፡

ዘጋቢው የደቡብ ኮሪያ የሺን የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ስራ አስኪያጁን ጠይቆ ኩባንያው የሚያመርታቸውን የስፖርት አልባሳት 60 በመቶውን ለአውሮፓ፣20 በመቶውን ለአሜሪካና ቀሪውን ለኢስያ ገበያ እንደሚያቀርብ ጠይቆ መረዳቱን በዘገባው አመልክቷል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ያሉት ኩባንያዎች የኢስያ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ፒቪኤች ያሉ አለም አቀፍ መለያ ያላቸው ልብሶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን ኢቢሲ ኢስያ ኒኬይን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ሐምሌ 10፣2009