ዜና ዜና

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሚሆን ገለጸ::

በተያዘው ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የታንዛንያ፣ አይቮሪኮስት እና ሴኔጋልን አስከትሎ በተያዘው ዓመት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሚሆን የዓለም ባንክ ትንበያ   አመለከተ፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት 8 ነጥብ 3፣ ታንዛንያ 7 ነጥብ 2፣ አይቮሪኮስት 6 ነጥብ 8 እንዲሁም የሴኔጋል 6 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ የዓለም አቀፉ የኢኮኖሚክ ትንበያ በያዝነው ወር ላይ ባወጣው ትንበያ አመልክቷል፡፡

እንደዓለም ባንክ ገለጻ ፤አገራቱ በመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት፣ የግብርና ምርት ዕድገትና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መስፋፋት ለተመዘገበው ዕድገት ዓይነተኛ ምክንያት ተደርገው ተወስደዋል፡፡ 

አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት በተያዘው ዓመት 2 ነጥብ 6 እንዲሁም በቀጣዩ ዓመት 3 ነጥብ 2 ኢኮኖሚያዊ እድገት እነደሚኖራቸው ባንኩ ጠቁሟል፡፡ 

አነስተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አገራትና የምስራቅ አፍሪካ አገራት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ስጋት እንደሚኖራቸው አመልክቷል፡፡

በተጨማሪም በምስራቅ አፍሪካ አገራት እየተከሰተ ያለው ድርቅ ምርታማነትን በመቀነስ፣ የምግብ ዋጋ በማናር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እክል እንደሚሆን ነው የገለጸው ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታም ኢትዮጵያ የኬንያን የኢኮኖሚ ዕድገት በመብለጥ የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ቁንጮ ላይ እንደምትገኝ አይ ኤም ኤፍ በሚያዚያ ወር 2009 ዓመተ ምህረት ባወጣው መረጃ መገለጹን ጠቅሷል ፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የኢኮኖሚ የ29 ሚሊየን ዶላር ያህል ልዩነት እንዳለው በመጥቀስ ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከኬንው በእጥፍ ያህል የሚበልጥ በመሆኑ ለኢኮኖሚያው ዕድገት ልዩነቱ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደዳለው ባንኩ አስረድቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላቸው ንቁ ተሳትፎና የውጭ ባለሐብቶች በዋናነትም የቻይና ባለሐብቶች በሀገሪቱን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ ማድረጋቸው ኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ የመሪነት ደረጃ ላይ እንድትቆናጠጥ ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ መሆኑን ነው የተመለከተው ሲል አፍሪካ ኒውስን ጠቅሶ ኢ.ቢ.ሲ. ዘግቦታል ፡፡

አዲስ አበባ ሀምሌ 9/2009 (ኢ.ቢ..ሲ)