ዜና ዜና

የኢፌዲሪ የመከላከያ ሚኒስትር ከኳታር አቻቸው ጋር ተወያዩ፡፡

የኢፌዲሪ የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሳ ከኳታር አቻቸው ዶክተር ካሊድ ቢን ሞሃመድ አቲያህ ጋር መክረዋል፡፡

ሁለቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች በኳታር ባደረጉት ምክክር በሀገሮቻቸው የጋራ ጥቅም ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት በሚጠናከርባቸው ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው ተጠቁሟል፡፡

ኳታር በአሁኑ ወቅት ሰዓኡዲ ዓረቢያ እና ግብፅን ጨምሮ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡

ሳዑዲ እና አጋሮቿም ኳታርን ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች በሚል ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ነው፡፡

ኢትዮጵያም የኳታር እና የባህረ ሰላጤው ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ  በውይይት እንዲፈታ ድጋፏን እየገለፀች ትገኛለች፡፡

ከኢትዮጵያ ባሻገር አሜሪካ እና ኩዌት የዓረብ ሀገራቱን የሻከረ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት ለመቀልበስ ድርድርን ቀዳሚ አድርገዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)