ዜና ዜና

የወጣቶችን ተዛዋዋሪ ፈንድ ወደስራ ለማስገባት የሚያስችሉ አሰራሮችን እየተዘረጋ ነው- የአ.አ ከተማ አስተዳደር

የወጣቶችን ተዛዋዋሪ ፈንድ ጥቅም ላይ ለመዋል የሚያስችሉ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ከፌዴራል መንግስት የሚያገኘውን ና የራሱን ድርሻ ለተዘዋዋሪ ፈንድ በመመደበብ የአፈፃፀም አቅጣጫ ማስቀመጡን የከተማው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወርጃሞ ብሩ ተናገረዋል፡፡

በዚህም አስተዳደሩ የራሱን ካፒታል በመመደብ ጭምር የከተማው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በበላይነት እንዲመራው ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

አቶ ወርጃሞ እንዳሉት የተዘዋዋሪ ፈንድ ለስራ አጥ ወጣቶች ብቻ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡

በከተማ ደረጃ የሚመደበውን የወጣቶች ፈንድ በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም በኩል ተደራሽ እንደሚደረግም አቶ ወርጃሞ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ 25 ሺህ የሚገመቱ ማህበራት በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው ስራ ላይ እንደሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

ግንቦት 11፣2009/ኢቢሲ/