ዜና ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲንጋፖር በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ ከሰኔ አንድ 2017 ጀምሮ ወደ ሲንጋፖር በረራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

አየር መንገዱ አዲስ ለሚያደርገው በረራ አልትራ ቦይንግ 787 እንደሚጠቀም የተገለጸ ሲሆን ከሲንጋፖር ቱሪዝም ቦርድ ጋር በትብብር ይሰራልም ተብሏል፡፡

አየር መንገዱ በቀጥታ በሚያደርገው በረራ በአፍሪካና በሲንጋፖር መካከል እየጨመረ የመጣውን የተጓዦች ፍላጎት ለማሟላት ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ወደ ሲንጋፖር የሚደረገው በረራ በኢትዮጵያ ብሎም በአህጎሪቱና በሲንጋፖር መካከል የንግድ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲጎለብት ያስችላል ፡፡

አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2025 በተለያዩ የአለም ሀገራት 120 የበረራ መዳረሻዎችን ለመዘርጋት አቅዶ እየሰራ መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል

ግንቦት 11/2009 /ኢዜአ/