ዜና ዜና

በተመድ የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ዶ/ር ቴድሮስን እንደሚደግፉ ገለጹ

ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት እየተወዳደሩ የሚገኙትን ኢትዮዽያዊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የማይዋዥቅ ድጋፍ እንዳላቸው የተመድ የአፍሪካ ተወካይ ቴቴ አንቶንዩ ገለጹ፡፡

በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ቡድን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ከአምስት ቀን በኋላ አመታዊ የአለም የጤና ቀን ስብሰባ በሚካሄድበት በግንቦት 15 እንደሚከናወን ይጠበቃል᎓᎓

የአፍሪካ የአምባሳደሮች ቡድን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ቢመረጡ በአለም የጤና ጅርጅት የሚፈለገውን አዲስ ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል᎓᎓

ዶክተሩ ሳይንሳዊና ዲፕሎማሲያዊ ክህሎት እንዳላቸውና የእርሳቸውን የምረጡኝ ዘመቻ ከጎን ሁነው እንደሚደግፉ አረጋግጠውላቸዋል᎓᎓

ከኢትዮዽያ፣ ከሞዛምቢክ፣ ከቻድ ከሩዋንዳ ፣ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐፕሊክና ከማሊ የተውጣጡ አምባሳደሮች አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ከአፍሪካ አንድም ሰው ተመርጦ እንደማያውቅና ይህ ሁኔታ ግን በዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መቀየር እንዳለበት ገልፀዋል᎓᎓

ግንቦት 10፣ 2009/ኢቢሲ/