ዜና ዜና

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በጽ/ቤታቸው መግለጫ ሰጡ።

መግለጫዉ በሀገሪቱ በተካሄደዉ የጥልቅ ተሀድሶ፤በወጣቶች ስራ ፈጠራና እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት ላይ ትኩረት አድርጓ፡፡

የተሃድሶ እንቅስቃሴ ከተካሄደ በኋላ የህዝብ ንቅናቄ ምን ደረጃ ላይ ነው?መንግስት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ያደረገው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ- የተሃድሶ እንቅስቃሴ ሲካሄድ ዋና ግብ ተደርጎ የተወሰደው በሥራዎቻችን ዘንድ የውጤት ማነስና በህዝብ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎችንና ፍላጎቶችን እርካታ በሚያስገኝ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ነው። በዚህ መሰረትም የተለያዩ የለውጥ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ከነዚህም መካከል ከህዝቡ ቅሬታ የቀረበላቸውን የሥነ ምግባርና የአመለካከት ችግር ያለባቸውን አፈፃፀማቸውንና የተሻሉ የተባሉትን አመራሮች የመተካት ስራ መከናወኑን ገልፀዋል። ስለዚህ በጥልቀት የመታደስ ተግባሩ በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ መሆኑን ጭምር በመግለጫቸው አመልክተዋል።

የተተኩት አመራሮችም ብቁ እንዲሆኑ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። ዕቅድም ወስደው ወደ ትግበራ ገብተዋል ብለዋል። ነገር ግን ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚፈለገውን ውጤት አስገኝቷል ማለት እንደማይቻል ጨምረው ተናግረዋል። በመሆኑም ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር ተስፋ ሰጪ ጅምሮች እንዳሉ አመልክተው የሚፈለገው ደረጃ ላይ ባለመድረሱ ቀጣይ ሥራ ይጠይቃል ብለዋል። ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችም የተመለሱም ያልተመለሱም እንዳሉ አውስተው በዚህ ተስፋ ሰጪ ውጤት መምጣት ቁጥጥር የሚያደርጉ ተቋማትንም ጠቅሰዋል። የህብረተሰቡ ተወካዮች ም/ቤት እና በየደረጃው ያሉ ም/ቤቶች ከፍተኛ አስትዋጽኦ አድርገዋል። በተመሳሳይም የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የሰባዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዮችን በጥልቀት መመርመርና ሪፖርት በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

ወጣቶች፦ የወጣቶችን የሥራ እጥነት ችግር በመቅረፍ ከትሬዥሪ ፈንድ / Treasury fund / የ10 ሚሊዬን ብር ተመድቦ እየሰራ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም በጥልቀት የመታደስ ወቅት አንዱ ፈጥኖ ምላሽ እንዲሰጠው እንደ ግብ ተደርጎ ከተወሰደ ጉዳይ አንዱ ነው። ሌሎች የገንዘብ ምንጮች እንዳሉ ሆኑ ከትሬዥሪ የ10 ሚሊዬ ብር ተመድቦ ስራውን ጀምሯል ብለዋል።

የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ በከፍተኛ አመራር የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሌት ተቀን ክትትል እየተደረገበት ያለ ሥራ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፈንዱ ደርሶ በጀመረባቸው አካባቢዎች ጥሩ የተሰሩ እንዳሉ ገልፀው ያልጀመሩት ከጀመሩት ተሞክሮ ወስደው ወደ ሥራ መግባት አለባቸው ብለዋል። ይህም በወጣቶች ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልፀው ለወጣቶች ሥልጠና ወስደው የቢዝነስ ዕቅድ አዘጋጅተው በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ገብተው እየሰሩ አንዳሉ አመልክተዋል።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች በደረሰው ሁከትና ግርግር በህዝብና በንብረት ላይ የደረሰውን ጥፋተ አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሪፖርት አቅርቧል። ሪፖርቱም በጥልቀት የታየና የተጠና መሀኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ከሪፖርቱ ለመረዳት እንደሚቻለው ብዙ ዜጎች ለህልፈተ ህይወት፣ ለከፍተኛ ንብረት ውድመት ምክንያተ መሆኑን ተመልክቷል። የሰባአዊ መብት ኮሚሽን አሁን ባለበት አቅሙ እየተጠናከረ መጥቷል። ለዚህም እንደ ምክንያተ የሚነሳው የሁከቱንና የብጥብጡን ጉዳዮች አጣርቶ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲፀድቅ ማድረጉ እንደማሳያነት ጠቅሰዋል።

"በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተጠያቂ በሆኑ አካላት ላይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል።"- ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከጋዜጠኞች ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ እንደተናገሩት፤ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ሁከትና ብጥብጥ በተፈጠረበት ወቅት የተሳተፉ አካላት በሪፖርቱ በግልጽ ተለይተው ቀርበዋል። በዚህ መሰረትም መንግስት ተጠያቂ የሆኑ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ገልፀዋል። ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የተወካዮች ም/ቤት የኮሚሽኑን ሪፖርት ውሳኔ ሲያሳልፍ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም እንደተናገሩት ከኮሚሽኑ ሪፖርት በሀገሪቱ የተጠያቂነት ደረጃ ከፍ እያለ መምጣቱን ያመለክታል። ይህም የሰብአዊ መብት ጥበቃ አቅሙን በእጅጉ እያጎለበተ መምጣቱን ያረጋግጣል። ይህም የጥልቅ ተሃድሶ አንዱ ወጤት ነው ብለዋል።

የውጭ አጣሪዎች እንዲገቡ መንግስት ያልፈቀደበት ዋናው ምክንያት የሀገር ውስጥ ተቋማትን የመመርመር አቅም ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ገልፀዋል።

የጥልቅ ተሃድሶ ዋና ግብም የቁጥጥር ተቋማት አቅም እንዲጎለብት ነው ብለዋል። የጥልቅ ተሃድሶው ከተካሄደ በኋላ የተወካዮች ም/ቤት፣ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የኢፌዴሪ ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጥልቅ ተሃድሶው ውጤት እንዲያመጣ ቁጥጥር በማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

12/08/09