ዜና ዜና

የጥልቅ ተሀድሶዉ መስመር በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ አመኔታ ፈጥሯል- ጠቅላይ ሚነስተር ሀይለማሪም ደሳለኝ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ በወቅታዊ እና  ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ  ለጋዜጠኞች በፅህፈት ቤታቸዉ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በአገራዊ የተሀድሶ እንስቃሴን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ሲመልሱ የጥልቅ ተሀድሶዉ መስመር በህዝብ ዘንድ አመኔታ አስገኝቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የጥልቅ ተሀድሶዉ መስመር የአስፈፃሚ አካላትን ለመቆጣጠርና አቅም ለማጎልበት ረድቷል፡፡የድሞክራሲን ስርአትን የበለጠ ለማጎልበት ብሎም  የመድበለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ ለማካሄድ ያግዛል ብለዋል፡፡

በዚህ ወቅት በአገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ከፍተኛ እርብርብ እየተደረገ ይገኛል በመሆኑም የወጣቶች ፈንድ ተመድቦ እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተዉ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

በሀገሪቱ ዉስጥ የዉጭ ምንዛሬ እጥረት መከሰቱ በማምረቻ ዘርፉ ላይ ያለዉን አሉታዊ ጎን በተመለከተ  ለተነሳላቸዉ  ጥያቄ ሲመልሱ እጥረቱ የአጭር ጊዜ  አይደለም ሆኖም የመንግስት ዋና ትኩረት የዉጭ ምንዛሬ እጥረቱ እድገታችንን የማይገታ ማድረግ ነዉ ብለዋል፡፡

በዉጭ አገራት የሰራ ስምሪትን በተመለከተ ሲገልፁ በቅድሚያ ኢትዮጰያዉን ለዉጭ አገር የስራ ስምሪት ከሚሄዱቸዉ አገራት ጋር ስምምነት ይደረጋል፡፡እንዲሁም ዜጎች ለስራ ወደ  ዉጭ አገር ከመሄዳቸዉ በፊት ተገቢዉን ክህሎትና ቋንቋ ችሎታ እንዳዳብሩ ይደረጋል፡፡

ከስደታኛ አያያዝና አቀባበል በተመለከተ ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ሲመልሱ ኢትዮጵያ በአለም ሁለተኛ የስደተኛ ተቀባይ አገር መሆኑዋን አዉስተዉ ስደተኞች በአገሪቱ ዉስጥ በበግብርና አዲስ በሚገነቡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ ተሰማርዉ እራሳቸዉን እንዲጠቅሙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከግብፅና የባህረ ሰላጤዉ አገራት ጋር በተያያዘ ለተሰነሳዉ ጥያቄ ሲመልሱ የኢትዮጵያና ግብፅ ግንኙነት በትክክለኛዉ መስመር ይገኛል፡፡ኢትዮጵያን የሚጎዳ ማንኛዉም  ተግባር በግብፅ ምድር እንደማይፈፀም የግብፅ ባለስልጣናት እንዳረጋገጡላቸዉ ገልፀዋል፡፡

በተያያዘም ግብፅ በበርበራ ወደብ የጦር ሀይል እስቀምጣለች የሚባለው መሰረት የሌለዉ መረጃ መሆንኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትየጵያ ከባህረ ሰላጤዉና መካከለኛዉ ምሰራቅ ሀገራት ያለት ግንኑነት የሀገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያመጣዉ እንጂ ከሌላ አጀንዳ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተደጋጋሚ ጊዜ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳዎች በጋምቤላ የሚደርሱትን ጥቃት በአጭር ጊዜ ለማፍታት የደቡብ ሱዳን አለመረጋጋት እንቅፋት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሌላዉ ሀገራቱ የ1000 ኪ.ሜ በላይ የሚረዝም ድንበር ያለቸዉ መሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

ይሁንጂ የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በስፍራዉ እንዲሰፍር ተደርጓል ብለዋል፡፡

 በሌላ በኩል በጋምቤላ ክልል ለበርካታ አመታት መሬት ተቀብለዉ ያላለሙና ወደ ስራ ገብተዉ ወደ ሚጠበቀዉ ደረጃ ዉጤት ላይ ያልድረሱ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡

በኦሮሚና ኢትዮጰያ ሶማሌ ክልል በተከሰተዉ የድንበር ግጭት በተለከተ ሲገልፁ ግጭቱ በወሰን ማካለል ችግር ሳይሆን ይህን እንደምክንያት ለመጠቀም በሚፈልጉ ሀይሎች የተነሳ ነዉ ብለዋል፡፡ ክልሎቹ የወስን ማካለል ስራ ለማከናወን ከስምምነት ደርሰዋል ብለዋል፡፡

11/08/09