ዜና ዜና

የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች የዜጎችን መብቶች እንዳይጥሱ እየተቆጣጠርኩ ነው - የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

እየተገነቡ ያሉና በቀጣይ የሚገነቡ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በህግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶችን እንዳይጥሱ ለመቆጣጠር የሚያስችል ስራ እያከናወንኩ ነው አለ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም።

ተቋሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

በዚህም ተቋሙ በግንባታ ላይ ያሉና ተገንብተው የተጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ስራዎች የዜጎችን መብት ስለመጋፋትና አለመጋፋታቸው የሚያረጋግጥ ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።

ጥናቱን መሰረት ያደረገ የመፍትሄ ሀሳቦችም ተቀምጠዋል ተብሏል።

ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ቤቶች ግንባታ ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን ለመቆጣጠር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ነው ተቋሙ ያስታወቀው።

ውይይቱ ከስአት በኋላም የሚቀጥል ሲሆን ተቋሙ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)