ዜና ዜና

በግድቡ ላይ ጥናት የሚያካሄዱ ኩባንያዎች በወጣላቸው የጊዜ ሰሌዳ ጥናቱን እያካሄዱ መሆኑ ተገለፀ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ሁለት ቴክኒካዊ ጥናት የሚያካሄዱ ኩባንያዎች በወጣላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ጥናቱን እያካሄዱ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና የኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ ከባለፈው ወር አጋማሽ ጀምሮ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በደረሱት ስምምነት መሰረት ጥናቱ እየተካሄደ ነው።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ አያያዝና አለቃቀቅ እንዲሁም ግድቡ በታችኛው የተፈሰሱ ሀገራት ላይ የሚኖረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ነው በኩባንያዎቹ የሚጠናው።
የጥናቱ ስራ በተያዘለት ጊዜ እየተካሄደ መሆኑንም ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል።

በኩባንያዎቹ የእስካሁኑ ስራ ላይ ሶስቱ ሃገሮች ተገናኝተው በቅርቡ ውይይት እንደሚያደርጉም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ቢ.አር.ኤል እና አርቴሊያ በተሰኙ ኩባንያዎች የሚጠናው ጥናት በ11 ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለሶስቱ ሃገራት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
የጥናቱ ውጤት በግድቡ ግንባታ ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንደለሌ ከዚህ ቀደም መገለጹ ይታወሳል።

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)