ዜና ዜና

መንግስት 1 ቢሊዮን ብር በመመደብ የምላሽ ስራ እየሰራ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ

መንግስት የመሪነት ሚናውን በመውሰድ 1 ቢሊዮን ብር በመመደብ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦት የምላሽ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠ/ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡ የክልል መንግስታትም በራሳቸው በጀት በመመደብ የምላሽ ስውን እያከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ይህን ያሉት  የመንግስት የ6 ወር አፈጻጸምን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው፡፡

በ2009 ዓ.ም ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ አቅርቦት  948 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሚያስፈልግ ተለይቷል ብለዋል፡፡

ጠ/ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ እነደገለጹት የእርዳታ አቅርቦቱ ካባለፈው አመት የዞረና በዚህ አመትም የተመደበውን ሀብት በመጠቀም ለአርብቶ አደርና ቆላማ ወረዳዎች ቅድሚያ በመስጠት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

በመሆኑም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስና  በእንስሳት ሀብት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ከፍተኛ ጉድለት ማቃለል ተችሏል ብለዋል፡፡

 አክለውም እስካሁን ድረስ እየተደረገ ያለው ጥረት በአርብቶ አደሮቸ አካባቢ ያለውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል የሚመጥን እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ክትትል እተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሀገራችን የተከሰተውን ድረቅ አደጋ በመመከት ረገድ የመንግስት፣ የህብረተሰቡና የግል ባለሀብቱ ደርሻ  የጎላ መሆን ስላለበት አገራዊ አቅምን አሟጦ ለመጠቀም ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባናል ነው ያሉት፡፡

 መጋቢት 11፣2009 ዓ.ም