ዜና ዜና

“ ድርቅን የመከላከል አቅማችን አድጓል”- ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ

ጠ/ሚኒስትር ሀ/ማይያም ደሳለኝ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ አመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ የቀረበላቸውን ጥያቄ ሲመልሱ "በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ድርቅን የመከላከል አቅሟ በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡" ብለዋል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምንም የሰው ህይወት እንዳይጠፋ መደረጉን የተናገሩት ሚኒስትሩ በቀጣይም በድርቅ ምክንያት ሞትና ረሀብ እንዳይኖር የማድረግ አቅም አለን በማለት ተናግረዋል፡፡

ውኃን የመያዝና የመጠቀም ችሎታችንን ማሳደግ ፣ በቆላማ አካባቢዎች የምርት ዘርን የማስፋፋት ስራ መስራትና የመኖ አቅርቦት ጉዳይ ትኩረት የምንሰጣቸው ሲሆን የክምችት ስራ እና መጋዘንም ሊኖረን ይገባል ሲሉ አፀንኦት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡

ድርቁ በተከሰተባቸው ወረዳዎች ውስጥ የአመራር ክፍተት መኖሩን ያልሸሸጉት ሚኒስትሩ ችግሩ የተከሰተው ከአቅም ውስንነት ጋር በተያያዘ ስለሆነ ለመፍትሄው በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡ ፡

በአጠቃላይ ሰዎችና እንስሳት ለረሀብ እንዳይጋለጡ የማድረግ አቅም ሀገሪቱ መገንባቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡ ፡