ዜና ዜና

"በአዲሱ የገቢ ግብርና ታክስ አስተዳደር አዋጅ ዙሪያ የተሰጣቸው ሥልጠና ስራቸውን ባግባቡ እንዲያከናውኑ ጠቃሚ እውቀቶች ያገኘንበት ነው " - የሐረሪ ክልል የገቢዎች ባለስልጣን ሰራተኞች

በሐረሪ ክልል የገቢዎች ባለስልጣን ከአዲሱ የገቢ ግብርና ታክስ አስተዳደር አዋጅ ጋር በተያያዘ በስሩ ያሉ ፈፃሚዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው በዋናነት በአዲሱ የገቢ ግብርና ታክስ አስተዳደር አዋጅ ዙሪያ በተሻሻሉ፣ በተካተቱ እንዲሁም በከፊል በተካተቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዳደረገና ይህም በቂ እውቀት አግኝተው ለመተግበር እንደሚረዳቸው በስልጠናው የተሳተፉ የተቋሙ ሰራተኞች ገልፀዋል፡፡

የአዋጁ ዋና አላማ የግብር ከፋዩን እንግልት ለመቀነስ እና መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዲያገኝ ማስቻል መሆኑን የጠቀሱት ሰልጣኞች፤ ሰራተኛው ስራውን ጠንቅቆ እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ አሻሚ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ባግባቡ እንዲመለስ ለማድረግ እያንዳንዱ ግብር ከፍይ ሳይንገላታ ለማስተናገድ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ አጠቃላይም ከአዲሱ የገቢ ግብርና ታክስ አስተዳደር ጋር በተያያዘ ያገኙት ስልጠና ባለሙያው የታክስ አስተዳደሩን በፍትሃዊነት እንዲመራ ያደርጋል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ህብረተሰቡ ደረሰኝ የመቀበል ባህሉን እንዲያዳብር መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
መጋቢት 11/2009