ዜና ዜና

የደ/ብ/ብ/ክ/መ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የክልሉ መንግስት  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቆሼ በቆሻሻ መደርመስ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸዉ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

አቶ ሰለሞን ሃይሉ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ የደረሰውን አደጋ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የክልሉ መንግስት በደረሰው አደጋ እጅግ ማዘኑን እና በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በክልሉ መንግስት ስም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ለተጎጂዎች የተሰጠውን ድጋፍ አስመልክተው እንደገለጹት የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚሆን የ5 ሚሊዮን ብር የ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንና ተጎጂዎቹን ለማቋቋም በሃገር ደረጃ ለሚደረገው ጥረት በቀጣይም የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 7/ 2009 የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት