ዜና ዜና

የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በማሰፋፋት የመዋቅራዊ ሽግግሩን ለማፋጠን ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው-ጠ/ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ማልማት የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሰፋፋት፤ የመዋቅራዊ ሽግግሩን ለማፋጠን ፤ሰፊየስራ እድል ለመፍጠርናየቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማምጣት የተሸለ አማራጭ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ይህን ያሉት  የመንግስት የ6 ወር አፈጻጸምን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው፡፡

 በአለም አቀፍ ደረጃ በምርታማነት በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆኑ ቀላል የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ለዘርፉ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ክላስተሮችን በማልማት ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አዳዲስ ቴክኖለጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እየተደረገ ነው፡፡ስለዚህየኢንዱስትሪ ምርቶችን ባገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬ ገቢያችን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት ፡፡

ሚኒስቴሩ  የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ንሁስ ዘርፍ በተለይም  ለከፍተኛና መካከለኛ ማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው አስተማማኝ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ እንዲሆን የተጀመረው ስራ ገና ወደሚፈለገው ደረጃ ያልደረሰ መሆኑ በውል እታየ ነው፡፡ በመሆኑም ከባድ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ የኬሚካልና የፋርማስቲካል ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋትና ከቀላል ኢንዲስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር  ተመጋጋቢ ሆነው እንዲፈፅሙ ለማድረግ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል በማለት አብራርተዋል፡፡፡፡ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ የኢንዱስትሪው ዘርፍ አፈፃፀም በሚታይበት ጊዜ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ  መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡በመካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ አፈጻፀሞች ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል ፡፡

 

የፓርኮች ግንባታ እንዲፋጠንና የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ባለሀብቶች ገብተው ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡