ዜና ዜና

ቦሪስ ጆንሰን የአየር መንገዱን ዕድገት አደነቁ

የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈጣን እድገት እንዳስደነቃቸው ገለጹ᎓᎓

ሚንስትሩ ይህን የተናሩት በአፍሪካ ትልቁንና ዘመናዊ የሆነውን የአየር መንገዱን የአቪዬሽን አካዳሚን በጎበኙበት ወቅት ነው᎓᎓

"የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለማችን ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አየር መንገዶች አንዱ ነው ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፡፡

በዚህም እንግሊዝ ከአየር መንገዱ ጋር በጋራ በመስራቷ ኩራት እንደሚሰማቸውም ጠቁመዋል፡፡

ጉብኝታቸው የኢትዮጵያንና የእንግሊዝን ወዳጅነት የሚያጠናክር ነው ሲሉ ጠቁመዋል᎓᎓

የኢትዮዽያ አየር መንገድ በአሁኑ ጊዜ ወደ ታላላቅ የአውሮፓ ከተሞች የሚበር ሲሆን ለንደን፣ ብራስልስ፣ ደብሊን፣ ፍራንክፈርት፣ ማድሪድ፣ ሚላን፣ ፓሪስ፣ ሮም፣ ስቶክሆልምና ቬና ይጠቀሳሉ᎓᎓

አየር መንገዱ ወደ ኦስሎ መጋቢት 26፣ 2009 በረራ እንደሚጀምር ከአየር መንገዱ ድረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢቢሲ፣ መጋቢት 8/2009