ዜና ዜና

ሃገሪቱ የምትፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል አቅርቦት በቀጣይነትና በጥራት ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው-ጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ

የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ  ውጤታማነትን ለማሻሻል፣ ጥራትን ለማስጠበቅና ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል አቅርቦት በቀጣይነትና በጥራት ለማቅረብ የሚስችሉ መሰረታዊ ስራዎች እተሰሩ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ሚንስትሩ የመንግስትን የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት  የትምህርትና ስልጠና የቀጣይ  የ15 አመት ፖሊሲ  አቅጣጫ ጠቋሚ ፍኖተ ካርታ የማዘጋጀት ስራ በሂደት ላይ ይጋኛል፡፡

በቅድመ መደበኛ /መዋለ ህፃናት/ ና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎ ላይ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የዘርፉ እቅድ አፈፃፀም  መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማሪያም አገላለጽ ባለፈው አመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋትና ተጨማሪ ግንበታዎችን የማካሄድ ስራ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሙያ ደረጃና ብቃት ምዘና፣ በአሰልጣኞች ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ፣ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር የተለየ ስራ ተሰርቷል ፡፡

አያይዘውም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በአገሪቱ ያሉ ዜጎች እኩል የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑና ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እድዲችሉ ተቋማትን በተለያዩ ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ እተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ነባር ተቋማት በመደበኛ ፕሮግራም 136 ሺ ተማሪዎች የተመደቡ ሲሆን የተቋማትን የመቀበል  አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የአስራ አንዱ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች ግንባታ  42 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ሚንስትሩ አስረድረዋል፡፡

በዚህ የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከገቡ አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል የሴቶች ተሳትፎ 42 በመቶ  የደረሰ  ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ  በቅድመ -ምረቃ ፕሮግሞች ላይ  ያላቸውን የተሳትፎ ምጥጥን 40 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡ ከዚህም ሌላ የሴት መምህራንንና የአመራርነት ቁጥርና ድርሻ ለማሳደግ የተለያዩ ስልቶች ተነድፈው እተተገበሩ እንደሚገኙም ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል፡፡

መጋቢት 7/2009