ዜና ዜና

የልማት አርበኞች እውቅና መስጠቱ ሌሎች አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮችን ለተመሳሳይ ውጤት ያነሳሳል-የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢያሱ አብርሀ

ተሸላሚ አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች   የራሰቸውንና የቤተሰባቸውን ጉልበት በመጠቀም ፣ በግብርና የሚሰጣቸውን ምክረ ሀሳብ በመተግበር፣ ኣዲስ የግብርና ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ድህነትን በድል አድራጊነት አሸንፈዋል፡፡

በ8ኛው የአርሶ/አርብቶ አደር በዓል ላይ  የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢያሱ አብርሀ እንደገለጹት ባለፉት አመታት መንግስት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ህዝቡን በእየደየደረጃው ተጠቃሚ ያደረገ እድገት አምጥቷል፡፡ የአገሪቷን ህዳሴ ማረጋገጥ የሚያስችል እቅድ ነድፎ  ወደ ስራ በመግባት ባለፉት 12 ዓመታት ባለሁለት አሀዝ እድገትም  አስመዝግቧል፡፡

እንደሚንስትሩ ገለፃ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን  እቅድ ዘመን ግብርናው በየአመቱ በአማካይ የ8 በመቶ እድገት  እያሰመዘገበ ሄዶ በእቅዱ መጨረሻ እጥፍ እድገት የማስመዝገብ ግብ ተቀምጧል፡፡ አርሶ አደሮቹ የላቀ ዋጋ የሚያዎጡ ሰብሎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያመርቱ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ ምርት መገኘት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የልማት ቀጠናን ተከትሎ የማልማት አሰራር ዘዴን በመከተል  አካባቢዊ ፀጋዎች ላይ በመመርኮዝ ሜካናይዜሽን የእርሻ ስራን ተግበራዊ በማድረግ የተጀመረው ስራ ምርትና ምርታመነት ጭማሬ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም ቴክኖሎጅ የማስረጽ ስራን በማጠናከር አርሶ አደሩ እርስ በእርስ እንዲማማር እድል በመስጠት የእርሻ ስራን ለማዘመን ያስችላል፡፡ የግብርናውን ዘርፍ ወደ ኢንዱስትሪ መር ዘርፍ ለማሸጋገር ፈርጀ ብዙ ጥናቶች እየተደረጉ ነው፡፡ በ2ኛው የዕ.ት.ዕ ዘመን የምግብ ሰብሎችን ምርትና ምርታማነት መጨመር፣ የኢንዱስትሪ ግባትና የኤክስፖርት ሰብሎችን ምርት ማምረት፣ የሞዴል አርሶ አደሮችን ቁጥር ማሳደግ ትኩረት የተሰጣቸው ነጥቦች ናቸው ብለዋል፡፡

በቀጣይ አመታት የግብርና ግባት አቅርቦቶችን በተገቢው መንገድ መጠቀም፣ የአፈር ጥናትን መሰረት ያደረገ የማደበሪያ አጠቃቀምን በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ተግበራዊ ማድረግና  ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የሜካናይዜሽን እርሻ ግባቶችን በመቅረብና ገብያ መር የሰብል ምርቶችን የማምረት ስራዎች ልዩ ትኩረት እንደሚደረግባቸው ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ሌላ የቀጥታ የዘር ስርጭትን ማስፋፋት የግብርና ፍላጎቶችን አቅርቦት መሰረት ደረገ የመካናይዜሽን ግባቶችን ማቅረብ ፡፤ የገብያ መር የአመራረት ስርዓትን በመከተል በ4 ክልሎች በ25 ክላስተር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ተሞክሮ የማስፋፋት ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡ 

ከተፈጥሮ ሀብት ስራዎች በተጨማሪ እርጠበትን በማቀብ የተለያዩ የውሀ አመራጮችን  በመጠቀም  ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት እንቅስቃሴው ሰፊ ትኩረት ይሰጣል፡፡

የከተማ ግብርና እና የገጠር ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት  በ2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ሲሉ ሚንስትሩ አስገንዘበዋል፡፡

መጋቢት 3/2009 አዳማ