ታሪክ ታሪክ

ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን

 

ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ

በ20ኛው ምእት ሁለተኛው ሩብ ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ ኢትዮጵያን ከልጅ ኢያሱ በኋላ መምራት ጀመሩ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ሕብረት መቋቋም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

የኢትዮጵያ ነጻነት በጣልያን ወረራ ከ1936 እስከ 1941 እ.ኤ.አ. ድረስ ተቋርጦ ነበር። በዚህ ጥቃት ጊዜ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ በ1935 እ.ኤ.አ. በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ፊት የሚታወስ ንግግር በአማርኛ አደረጉ። ይህ ንግግር በዓለም ታዋቂ አደረጋቸው እንዲሁም በ1935 እ.ኤ.አ. በታይም መጽሄት «የዓመቱ ሰው» አስባላቸው። ጣልያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መሳተፍ ስትጀምር፣ እንግሊዝ ከኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ጋር ኢትዮጵያን ነጻ አወጣች። ግን እስከ 1943 እ.ኤ.አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር። በ1942 እ.ኤ.አ. ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባርነት እንደተከለከለ አወጁ።

ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ጀግና ሆነው ቢታዩም፣ የ1973 እ.ኤ.አ. ዓለምአቀፍ የነዳጅ ቀውስ፣ የምግብ ዕጥረትና የድንበር ጦርነቶች ተቃውሞ አስነሱ። ከዚያም በ1974 እ.ኤ.አ. በሶቪየት ሕብረት የተደገፈውና በመንግስቱ ኃይለ ማርያም የተመራው ደርግ ዓፄ ኀይለ ሥላሴን ከስልጣን አስወረደ።

የተለያዩ መፈንቅለ መንግሥቶች፣ የሰፋ ድርቀትና ስደተኞች የደርግ ሥርዓት ትልቅ ችግሮች ነበሩ። በ1977 እ.ኤ.አ. ሶማሊያ ኦጋዴንን በመውረሯ የኦጋዴን ጦርነት ተነሳ። በሶቪየት ሕብረት፣ ኩባ፣ ደቡብ የመን፣ ምስራቅ ጀርመንና ሰሜን ኮሪያ የመሳሪያ እርዳታ እንዲሁም ወደ 15 ሺህ በሚቆጠሩ የኩባ ወታደሮች ድጋፍ አማካኝነት ደርግ ኦጋዴንን እንደገና መቆጣጠር ቻለ።

በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቀይ ሽብር፣ የግዴታ ስደት፣ ወይም ረሀብ ሞተዋል። መንግስቱ ቀይ ሽብር ያካሄደው በተቀዋሚዎች በተፈጸመው ነጭ ሽብር መልስ እንደሆነ ጠቅሷል። በ2006 እ.ኤ.አ. መንግስቱ ኅይለ ማርያም በሌሉበት የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

በ1980ዎቹ መጀመሪያ የተከሰቱ ድርቀቶች ምክኒያት ስምንት ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ሲራብ፣ አንድ ሚሊዮን ደግሞ ሞተዋል። ተቃውሞ በትግራይና ኤርትራ ክልሎች ተስፋፋ። በ1989 እ.ኤ.አ. ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን መሠረተ። የሶቪየት ሕብረትም ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ መቀነስ ጀመረች። የኢኮኖሚ ችግሮች ተከሰቱ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተዳከመ።

በሜይ 1991 እ.ኤ.አ. የኢ.ህ.አ.ዴ .ግ. ጦር ወደ አዲስ አበባ አመራ። የመንግስት ሀይሎች ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ስላላገኙ፣ የኢ.ህ.አ.ዴ .ግ.ን ጥቃቶች መቋቋም አልቻሉም። መንግስቱ ኅይለ ማርያም ወደ ዚምባብዌ ሄደው እስከ ዛሬ ድረስ በዛችው ሀገር ይኖራሉ። ኢ.ህ.አ.ዴ .ግ. 87 አባላት ያሉት የሽግግር መንግሥት መሠረተ። በጁን 1992 እ.ኤ.አ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ እንዲሁም በማርች 1993 እ.ኤ.አ. የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት የሽግግር መንግሥቱን ለቀው ወጡ። በ1994 እ.ኤ.አ. ሁለት የሕግ አውጪ ምክር ቤቶችንና የፍትሕ ስርዓትን የሚደነግግ አዲስ ሕገ መንግሥት ተፃፈ። የመጀመሪያው ምርጫ በሜይ 1995 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በ1993 እ.ኤ.አ. በተካሄደውና የተባበሩት መንግሥታት በታዘበው ሕዝበ ድምፅ፣ ከ99 ከመቶ በላይ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብና በውጭ ሀገር የነበሩ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን መርጠዋል። በሜይ 24፣ 1993 እ.ኤ.አ. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች።

በሜይ 1998 እ.ኤ.አ. የድንበር ውዝግብ እስከ ጁን 2000 እ.ኤ.አ. ወደቀጠለው የኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት አምርቶአል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ጎድቶአል። በሜይ 15፣ 2005 እ.ኤ.አ. አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ተቃዋሚዎች ማጭበርበር እንደነበረ ወንጅለዋል። በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ200 በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። ግን አንዳንድ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባሎች ከምርጫው በኋላ ከነበረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው ነበር።

Pages: 1  2  3