የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ስልጣን እና ተግባር

 1. ለመንግስት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አመራር መስጠትና  በመስኩ መልካም አፈፃፀም የሚኖርበትን ስርአት መፍጠር
 2. ለፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የህዝብ ግንኙነት ስራ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና ማስተባበር
 3. የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞችን የአቅም ግንባታ ተግባሮችን ማከናወን፤ አጠቃላይ የስምሪት እና የእድገት አቅጣጫ መወሰን
 4. የመንግስት ቃል አቀባይ ስራዎችን ጨምሮ የመንግስት ኢንፎርሜሽን ዋነኛ ምንጭ በመሆን ማገልገል፤ የመንግስት መልእክቶችን መቅረፅ እና በልዩ ልዩ መንገዶች ማሰራጨት በሃገራዊ እና አለማቀፍ ጉዳዮች ላይ የመንግስትን አቋም መግለፅ
 5. የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን ፕሮግራሞችን ይዘት እና አፈፃፀም ማቀናጀት
 6. የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሚድያ የእለት ተእለት ዘገባ ቅኝት ስራዎችን በማከናወንና የህዝብ አስተያየት በማሰባሰብ መተንተንና ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት
 7. በመንግስት ፖሊሲዎች እና  በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመስጠት እና ግልፅነትን ለመፍጠር ህዝባዊ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ማስተባበር
 8. ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ህብረተሰቡን በአካል አግኝተው እንዲያነጋግሩ እና ተቋማትን በመጎብኘት የስራ ክንውኖችንና ሁነቶችን እንዲገነዘቡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
 9. በክልሎች ውስጥ የሚገኙ ኮሙዩኒኬተሮች ጋር ጠንካራ የግንኙነት ስርአት መፍጠር፣ እንዲሁም የአቅም ግንባታ መፍጠር
 10. የመንግስት የዌብሳይት ስራዎች መስራት
 11. ልዩ ልዩ የህትመት እና ኦዲዮቪድዮ ምርቶችን ማምረት፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የፎቶግራፍ እና የኦዲዮቪድዮ ቀረፃና የአርማ እና የህትመት ዲዛይንእንዲሰራላቸው ሲጠይቁ የማዘጋጀት እና የማማከር አገልግሎት መስጠት
 12. ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ሃገር ጋዜጠኞች በየወቅቱ መግለጫ መስጠት፤ ለጊዜያዊ ስራ ለሚመጡም ሆነ ተቀማጭነታቸው  ኢትዮጵያ ውስጥ ለሆኑ የውጭ ሀገር ዜና ወኪሎች ፈቃድ መስጠት
 13. ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአገር ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች በየጊዜው መግለጫ መስጠት
 14. ሀገሪቱ በውጭ አለም ልትታወቅበት በሚገባት ትክክለኛ ገፅታ እንድትታወቅ ሰፊ መረጃ መስጠት፤ በኢትዮጵያ ላይ የሚነዙ የተሳሳቱ መረጃዎችን መመከት
 15. በኮሙኒኬሽን ስራ ዙሪያ በሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ  ባለድርሻ ወገኖች መካከል በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የአጋርነት ስርአት መዘርጋት
 16. የሚድያ መሰረተልማት የሚያድግበትንና ብቃት ባለው ባለሙያ የታገዘና በኢትዮጵያ ብዙህነት ላይ የተመሰረተ ሚድያ እንዲገነባ ምቹ ሁኔታ መፍጠር
 17. በኮሙኒኬሽን፤ ኢንፎርሜሽንና ሚድያ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ማካሄድ
 18. ለሚሰጠው አገልግሎት እንደአስፈላጊነቱ በህግ መሰረት ክፍያ መሰብሰብ
 19. የንብረት ባለቤት መሆን፤ ውል መዋዋል በስሙመክሰስ እና መከሰስ
 20. አላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ፖ ሳ ቁጥር: 1364/530
ስልክ ቁጥር: +251-115-52-81-13
:+251-115-52-81-92
ፋክስ : +251-115-52-20-60
: +251-115-54-25-87
Follow Us
Facebook
google +
youtube
twitter
© 2016 የኢፌድሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት