ፖለቲካ ፖለቲካ

የኢትዮዽያ ፖለቲካ

አስተዳደራዊ ክልሎች

ከ1996 እ.ኤ.አ. በፊት ኢትዮጵያ በ13 ክልሎች ተከፍላ ነበር። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጽያ ውስጥ 9 አስተዳደራዊ ክልሎች ይገኛሉ። አወቃቀራቸውም በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት «በህዝብ አሰፋፈር፤ ቋንቋ፤ ማንነት እና ፈቃድ ላይ» ተመስርቶ ሲሆን ክልሎቹም ፦

 • የትግራይ ክልል
 • የአፋር ክልል
 • የአማራ ክልል
 • የኦሮሚያ ክልል
 • የሶማሌ ክልል
 • የቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል
 • የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
 • የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል
 • የሀረሪ ሕዝብ ክልል ሲሆኑ በተጨማሪም
 • አዲስ አበባ እና
 • ድሬዳዋ እራሳቸውን የቻሉ የአስተዳደር አካባቢዎች ሆነው ተዋቅረዋል።ደዚህ ላይ የሰፈነኑ መራጃዎችበመጠኑም ቢሆን የተስታካከላ ስላልሆን ቢስታካከል የተመረጠ ኆናል

ሕዝብ

ኢትዮጵያ ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሄረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች የኦሮሞ፣ የአማራ፣ እና የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የአገሪቱዋ ሕዝብ ቁጥር ክ3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚተዋልባት አገር ናት። የእስልምና እምነት ተከታዮች ከ25-30%፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከ60-65% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 10% የሚሆነውን ይይዛሉ።

ቋንቋዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ80 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት፡፡ በአሁኑ ወቅት በእብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች ወደ አራት ዋና ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። እነዚሁም

 • ኩሻዊ፦ ወደ 19 ቋንቋዎችን የያዘ
 • የአባይ-ሰሃራዊ፦ ወደ 20 ቋንቋዎችን የያዘ
 • ኦሞአዊ፦ ወደ 23 ቋንቋዎችን የያዘ እና
 • ሴማዊ፦ወደ 12 ቋንቋዎች የያዘ ናቸው።

ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ፣ ኩናማኛ፣ ጉሙዝኛ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ፣ ጋሞኛ፣ ከፋኛ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ስልጢኛ፣ ሀደሪኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ።
የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ ትግርኛ ና አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለዕለት ተዕለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ፖ ሳ ቁጥር: 1364/530
ስልክ ቁጥር: +251-115-52-81-13
:+251-115-52-81-92
ፋክስ : +251-115-52-20-60
: +251-115-54-25-87
Follow Us
Facebook
google +
youtube
twitter
© 2016 የኢፌድሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት