መልክአ ምድር መልክአ ምድር

ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ የአፍሪካ ቀንድ በመባል በሚታወቀው አካባቢ የምትገኝ ከአፍሪካ በቆዳ ስፋቷ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የምትገኘ አገር ናት፡፡ ዙሪያዋን አምስት አገሮች ያዋስኗታል፡፡ በምስራቅ በኩል ጅቡቲና ሶማሊያ፤ በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ ኤርትራ፤ በደቡብ ኬንያ እና በምእራብ ሱዳን ናቸው፡፡ ጠቅላላ የቆዳ ሰፋት 1.1 ሚሊዬን ካሬ ሲሆን በውስጧ 7000 ኪ.ሜ የሚደርስ ርዝማኔ ያላቸው አስር ትላልቅ ወንዞችና ወደ 7000 ካሬ ጠቅላላ ስፋት ያላቸው ሀይቆች አሏት፡፡

መልክአ ምድር

ኢትዮጵያ በውስጧ የተለያዩ መልክአ ምድር ያላት አገር ከመሆኗ በተጨማሪ የአየር ንብረት አፈር የእንስሳትና የዕፅዋት ስብጥር የሚስተዋልባት አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በጣም ከፍተኛ የሆኑ ተራሮች ከላያቸው ጠፍጣፋ የሆኑ አምባ የሚባሉ ኘላቶዎች ስምጥ የሆኑ ሸለቆዎች፤ ጥልቅ የወንዝ ሸለቆዎችና ሰፋፊ ሜዳዎች በውስጧ ይዛለች፡፡ ከባህር ጠለል በላይ 4620 ሜትር ከሚደርሰው ዳሽን ተራራ እስከ 148 ሜትር ከባህር ጠለል በታች እስከሆነው የዳሎል ዲኘረሽን ድረስ የሚሆን ልዩነት ያለው የከፍታና ዝቅታን የምታስተናግድ አገር ናት፡፡

ለም ከሆኑ መሬቶችና ተራሮች ምንም የማይታይባቸው ከሚመስሉ መሬቶች አንስቶ፣ ኢትዮጵያ በብዙ ገባሮችና ትላልቅ እንደ አባይ ተከዜ አዋሽ ኦሞ ዋቢ ሸበሌና ባሮ-አካቦ በመሳሰሉ ወንዞች የታደለች አገር ናት፡፡

ከሜዲትራንያን ምስራቃዊ መጨረሻ ተነስቶ፣ ደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኘው ሞዛንቢክ ድረስ የሚደርሰው ታላቁ የስምጥ ሸለቆ ኢትዮጵያን ለሁለት ከፍሏት ያልፋል፡፡

የአየር ንብረት

ኢትዮጵያ እንደ መልክአ ምድራዊ አቀማመጧ የአየር ንብረቷም በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ሁኔታ ይታዩባታል፡፡ የመካከለኛው ኘላቶ አካባቢ ብዙም የማይፈራረቅ አይነት ወይናደጋማ አይነት የአየር ንብረት ይታይበታል፡፡ ዝቅተኛው የአየር ንብረት በአማካኝ 60c ሲሆን ነገር ግን ወደ ቀይባህር በረሀ አካባቢ 600c የሚደርስበት ጊዜዎች አሉ፡፡ በብዙ የአገሪቱ አካባቢ በክረምት ወራት ይኸውም ሰኔ ሀምሌና ነሀሴ ውስጥ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ይመዘገባል፡፡

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር

የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት አንዴ) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ።

የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ ሆነ።

Pages: 1  2  

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ፖ ሳ ቁጥር: 1364/530
ስልክ ቁጥር: +251-115-52-81-13
:+251-115-52-81-92
ፋክስ : +251-115-52-20-60
: +251-115-54-25-87
Follow Us
Facebook
google +
youtube
twitter
© 2016 የኢፌድሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት