የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ፅ/ቤት አመሰራረት

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም የሚጀምረው ከ አንድ ክፍለዘመን በፊት ነው። የመጀመሪያው ጋዜጣ የተዘጋጀው በእጅ ፅሁፍ ነበር ይህም የህትመት መሳሪያዎች እስኪተዋወቁ ድረስ ቀጥሏል።የጣልያን ወራሪዎችን ከሃገር መባረርን ተከትሎ የፕሬስ እና የ ኢንፎርሜሽን መምሪያ በፅህፈት ሚኒስቴር ስር ተቋቋመ። በጊዜውም የህትመት እና የኤሌክትኖኒክስ ሚድያዎች በሃገሪቷ በስፋት ተሰራጭተው ነበር። ይሁንና በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መጣስ እና ጥብቅ የ ሴንሰርሺፕ ቁጥጥር የዘርፉን እድገት አቀጭጨውት ነበር። በሌላ በኩል የቴሌቭዝን ስርጭት የጀመረው ደግሞ በዚሁ ጊዜ ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ በ1964 አ.ም የማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቋቋመ ይህም ከሁለት አመት በኋላ የቱሪዝም ስራን ጨምሮ በድጋሚ ተቋቋመ። በዚህ አደረጃጀትም የዘውዳዊው ስርአት እስኪያከትም እና ወታደራዊው የደርግ ስርአት እስኪተካ ድረስ አገለገለ።

በወታደራዊ ደርግ ዘመነ መንግስት የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንደገና የማስታወቂያ እና ብሄራዊ አማካሪ ሚኒስቴር በመባል በ1975 አ.ም ተቋቋመ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስሪያ ቤቶች እንዲመራ ስልጣን እና ሃላፊነት ተሰጥቶት ነበር።  የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

  • የአብዮታዊ ኢትዮጵያ ድምፅ
  • የፕሬስ መምሪያ
  • የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
  • የጋዜጦች እና መፅሄቶች ስርጭት ኤጀንሲ
  • የሴንሰርሺፕ አገልግሎት

ይህም አደረጃጀት የደርግ መንግስት በኢህአዴግ እስከተወገደበት ጊዜ ድረስ ቆይታል። የደርግ አገዛዝ የሰዎችን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመጨፍለቅ የሚገዛ ስለነበር የመገናኛ ብዙሃንን እድገት ገድቦት ቆይቷል። ከደርግ ውድቀት በኋላ የሽግግር መንግስቱ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ የዲሞክራሲ ስርአቱ እንዲያብብ አድርጓል። ከእነዚህም ውስጥ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ማወጅ እና የሴንሰርሺፕ ስርአትን ማስቀረት ይገኝበታል። ይህም እርምጃ ብዛት ያላቸው የግል ጋዜጦች እና መፅሄቶች እንዲበራከቱ አስችሏል። በሽግግሩ መንግስት ጊዜ የማስታወቂያ ሚኒስቴር  የነበረው  የኢፌዴሪ የማስታወቂያ እና ባህል ሚኒስቴር በመባል እንደገና ተቋቁሟል በወቅቱም የአስተሳሰብ እና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ  መብት በህገመንግስቱ እንዲካተት ተደርጓል።

የኢፌዴሪ የማስታወቂያ እና ባህል ሚኒስቴር፤ የኢፌዴሪ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በመጨረሻም የመንግስትኮሙኒኬሽንጉዳዮችጽ/ቤት በመባል ከመጋቢት 2000 አ.ም ጀምሮ ሃላፊነቱን አየተወጣ ይገኛል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ፖ ሳ ቁጥር: 1364/530
ስልክ ቁጥር: +251-115-52-81-13
:+251-115-52-81-92
ፋክስ : +251-115-52-20-60
: +251-115-54-25-87
Follow Us
Facebook
google +
youtube
twitter
© 2016 የኢፌድሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት