ዜና ዜና

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በቴክኖሎጂ የተደፈገፈ ስራ ፈጠራ ላይ እንዲሰማሩ እንግሊዝ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ከሆኑት ሱዛና ሞርሄድ ጋር ኢትዮጵያና እንግሊዝ በቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

እንግሊዝ በቴክኖሎጂ ያላትን የካበተ ልምድ በመጠቀም የኢትዮጵያ ወጣቶች ቴክኖሎጂ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደሯ ተናግረዋል፡፡

የሞባይል ክፍያ ስርዓትን በኢትዮጵያ ለማሸጋገርም እንግሊዝ ፍቃደኛ መሆኗን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንሰቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት1/2011