ዜና ዜና

የአረጋውያን ቀን ተከበረ፡፡

የአረጋውያን ቀን በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ28ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ27ኛ ጊዜ የሚከበር ነው፡፡ የዘንድሮው የአረጋውያን ቀን የተከበረው "የኦሮሚያ አረጋውያን ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል ነው፡፡

የኦሮሚያ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ ሞሀመድ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር አረጋውያን የእውቀታችን መሰረት በመሆናቸው ልንከባከባቸው ይገባል ብለዋል፡፡

እንደዚሁም አረጋውያን ባላቸው ልምድና እውቀት በተለያዩ መንገዶች ለህዝባቸው እያደረጉ ያሉትን ምክርና ድጋፍ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ አረጋውያን በሀገራችን አሁን በተገኘው ለውጥ ጎን በመቆም እንዲሁም ወጣቶቻችን በመምከር የልማት ኃይል እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አስታውሰዋል፡፡

ህዝቡም የእውቀት ባለቤት የሆኑት አረጋውያንን በመንከባከብ ልምዳቸውን መጠቀም አለበት ተብሏል፡፡ መረጃው የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነው፡፡

ጥቅምት 1/2011