ዜና ዜና

በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ዛሬ ይጀምራል።

 

 

ትናንት ከቀትር በኋላ ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደሚጀምር ተገለፀ።

 

በመዲናዋ ከትላንት  መስከረም 3 ቀን 2011 ዓም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊዎችና  በከተማዋ ወጣቶች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የቀላል ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦር ነበር።

 

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የባቡር ትራንስፖርቱ አገልግሉቱን ለማስጀመር ከፖሊስ ጋር በመሆን መስመሮች እየተፈተሹ  ነው፤ በጥቂት ሰአታት ውስጥም ይሕው ስራ ተጠናቆ አገለግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተጠቁሟል።

 

የአዲሰ አበባ ቀላል ባቡር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ እንዳሉት፤ የመስሪያ ቤቱ የጥንቃቄና የደሕንነት ሰራተኞች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን መስመሮችን የመፈተሽ ተግባራትን እያከናወኑ ነው።

 

ይህም የሚሆነው በባቡር መስመሮቹ ላይ ጉዳቶች ደርሰው ከሆነ አደጋ ሳይፈጠር አስቀድሞ ለማወቅና ለመጠንቀቅ እንዲያመች በመሆኑ ሕብረተሰቡ በትእግስት እንዲጠብቅ ነው የጠየቁት።

 

"በሙሉ መስመሮች ላይ የሚካሄደው የፍተሻ ስራ ሲጠናቀቅ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል" ብለዋል።

 

   አዲስ አበባ መስከረም 4/2011