ዜና ዜና

በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተከስቶ የነበረው የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እየተቃለለ ነው ተባለ

በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተከስቶ የነበረው የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እየተቃለለ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአገር አቀፍ ደረጃ የስኳር መድኃኒትን ጨምሮ በርካታ መድኃኒቶች በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ አቅርቦቱ በቂ ባለመሆኑ ህሙማን ለችግር ሲዳረጉ ቆይተዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ፥ በአሁኑ ወቅት በውጭ ምንዛሪ እጥረት ተከስቶ የነበረው የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እየተቃለለ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት ይህንን ችግር ለማቃለለ በአሁኑ ወቅት እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች ውጤታማ እንደሆኑ የገለጹት ሚኒስትሩ በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ተጋርጦ የነበረውን
ችግር ለመፍታት ከውጭ ለሚገቡ መድኃኒቶች ቅድሚያ እንደተሰጠ ጠቁመዋል።

የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ከውጭ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመድኃኒት አቅርቦቱ በቂ እንዳይሆን ትልቁን ድርሻ እንደወሰደ ገልፀዋል።

በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት እና ከስኳር መድኃኒት ስያሜ ጋር ተያይዞ የነበረው የአቅርቦት ችግር በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ የተወገደ መሆኑን ዶክተር አሚር አስታውቀዋል።

አዲስ አበባ ነሀሴ ፣5፣ 2010፤ኢዜአ