ዜና ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተመረጠ፡፡

አየር መንገዱ ዕውቅናዉን ያገኘው በዓመቱ ባስመዘገበው ፈጣን ዕድገትና ትርፋማነት እንዲሁም ለአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ዕድገት ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ነው ተብሏል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ትላንት በእንግሊዝ ርዕሰ ከተማ ለንደን ተገኝተው የዕውቅና ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

ኢቢሲ ሀምሌ 12 ቀን 2010 አ.ም