ዜና ዜና

ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።

ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው።

ኢንጅነር ሀብታሙ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት የባለሥልጣኑ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በመሾማቸው ነው።

በሌላ በኩል የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አንዷለም አድማሴ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው ምክትላቸው የነበሩት ወይዘሮ ፍሬሕይወት ታምሩ ተክተዋቸዋል።

ሀምሌ 11/2010