ዜና ዜና

ቱርክ ከሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ኢንቨስትመንት በአገራችን እንዳላት ተገለፀ

በአገራችን ያሉ የቱርክ ኢንቨስትመንት ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላር እንዳላቸው ተገለፀ።

በቱርክ የኢፌዲሪ አምባሳደር አያሌው ጎበዜ ዴይሊ ሳባ ከተባለ የቱርክ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት የቱርክ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለነዋያቸውን የበለጠ ስራ ላይ እንዲያውሉ እንሰራለን ብለዋል።

በሁለቱ አገራት ረጅም አመታትን ያስቆጠረው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደነበር ጠቅሰው ይኸው ግንኙነት አሁንም የበለጠ በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አምባሳደር አያሌው ጎበዜ በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አህመት ሪዛ ድሚሬር ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በቅርቡ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አብራርተዋል።

ሰኔ7/2010/የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት