ዜና ዜና

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አልጋወራሽ በአገራችን ጉበኝት ያደርጋሉ

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አልጋወራሽ ክቡር ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በሀገራችን ከሰኔ 8 -9 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ።

አልጋወራሽ ሼክ ቢን ዛይድ አል ናህያን በቆይታቸው ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እንዲሁም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በጋራ ጉዳዮች፣ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ ይመካከራሉ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋኪ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ የመስክ ጉብኝትም ያደርጋሉ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።

የሀገሪቱ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለንዋያቸውን በተለያዩ መስኮች ያፈሰሱ ሲሆን በቀጣይም በግብርናና ቱሪዝም መስኮች እንዲሰማሩ ይፈለጋል።

ሰኔ7/2010/የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት