ዜና ዜና

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ በዳንጎቴ ስሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ግድያ የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡

የኢዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የሚስተር ዲፕ ካማራና ሁለት ኢትዮጵያውያን የስራ ባልደረቦቻቸው ግድያ አስደንጋጭም አሳዛኝም ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን አዳአ በርጋ ወረዳ የሚገኘው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ዲፕ ካማርና ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የስራ ባልደረቦቻቸው ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ሰዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት ነው ህይወታቸው ያለፈው።

ግድያው ለምንና በማን እንደተፈጸመ ምርመራ መጀመሩን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ጥፋተኞችን ለህግ የሚያቀርብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በምእራብ ሸዋ ዞን አዳአ በርጋ ወረዳ የሚገኘው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ፋብሪካው የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በማምረት አቅሙ ከኢትጵያ ትልቁ ነው፡፡

ግንቦት 9/2010/ኢዜአ/