ዜና ዜና

ኢትዮጵያና በተ.መ.ድ የሠላም ማስከበር እንቅስቃሴ ለመተባበር ተስማሙ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የሠላም ማስከበር ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ ጂን-ፒየር ለክሮክስ ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ ወቅት የኢትጵያና የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ተባብረው ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ምክትል ዋና ፀሀፊው የኢትዮጵያ የሠላም አስፈፃሚዎች ተልዕኮ የማስፈፀም ብቃት እና ቁርጠኝነትን አድንቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት በበኩላቸው የሠላም ማስከበር ዘመቻዎች ስኬት ተቋማትን የማጠናከር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች እንዲሳኩ አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል፡፡

ሚያዚያ8/2010/የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት