ዜና ዜና

ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ከአርጀንቲና አቻቸው ጋር ተወያዩ

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ዛሬ በጵ/ቤታችው ከአርጀንቲና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ አምባሳደር ፔድሮ ቪለግራ ዴልገዶ ጋር ተወያይተዋል።

ወ/ሮ ሂሩት ኢትዮጵያ በንግድ ፣በኢንቫስትመንት እና በእርሻ ልማት ከአርጀንቲና ጋር ተባብራ ለመስራት ትፈልጋልች ብለዋል ። ሁለቱ አገራት በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በጋራ በመስራት የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድጉ ተነግራዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደ አርጀንቲና በራራ እንደሚጀምር የተነገሩት ወ/ሮ ሂሩት ይህ የሁለቱን አገራት ንግድ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል።

የአርጀንቲና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።

 የካቲት6/2010፤ የው/ጉ/ሚ