ዜና ዜና

’ቋንቋ የባህል ማህደር፤ ባህል ደግሞ የዕውቀት ማህደር ነው’’ -ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ

በጅማ ዩንቨርሲቲ የስነ-ቋንቋ መምህር የሆኑት ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ ለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዋች በአዳማ ከተማ ለ3 ቀናት በተዘጋጀው የምክረ ሀሳብ መድረክ ላይ እንደገለጹት አንዱ ያንዱን ባህል አወቀ ማለት አንዱ ለሌላው ዘብ ይቆማል፡፡

ባህላችን ገና ያልተነካና ብዙ መሰራት ያለበት ከመሆኑም ባሻገር በባህል ውስጥ የኣኗኗር ዘይቤ ፣ፍልስፍናና ለችግሮችመፍትሄ የሚሆን ዕውቀት በውስጡ ይገኛልም ብለዋል።

አገሪቱ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች፣ባህሎች፣ወጎችና ቋንቋዎች ባለቤት የሆነችው ሃገራችን ኢትዮጵያ ባህሏና ወጓ እርስ በርሳቸው ተግባብተው ለሃገራዊ ዓላማ እንዲቆሙ ኢንተርካልቸራል ኮሚዩኒኬሽን በሚል ርዕስ በሰጡት ስልጠና ላይ አመላተክዋል።

ኢንተር ካልቸራል ኮሚዩኒኬሽን ወይም ባህለ ተግባቦት በሁለት ባህሎች መካከል የሚኖር መግባባት ፣መከባበርና መቻቻል መሆኑን አስረድተዋል። በቋንቋና በባህል መካከል ተግባቦት ሲኖር ነው ዜጎች ሀገራቸውን ማሳደግ የሚችሉት ብለዋል።

የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራርና ባለሙያዎች የብዙ ባህልና ቋንቋ ባለቤት የሆነውን ህዝብ በማቀራረብ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ዶ/ር ደመላሽ አሳስበዋል። ህብረተሰቡም በመንግስትና በህዝቡ መካከል እንደ ድልድይ ሆነው ለሚያገለግሉት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ተገቢውን ክብር መስጠት እንዳለበት በአፅኖት ተናግረዋል።

ባለብዙ ባህልና ቋንቋ ባለቤት ለሆነችው ለሃገራችን ባህለ ተግባቦት በመፍጠር በኩል ምሁራን ብዙ እየሰሩ እንዳልሆነ የተናገሩት ዶ/ር ደመላሽ ፤ይህንን ችግር ለመቅረፍ የጅማ ዩኖቨርሲቲ intercultural communication and public diplomacy የሚል ዲፓርትመንት ከፍቶ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተርስ ደረጃ በማስተማር ላይ ይገኛል ።

ወደ ፊትም በግልም ይሁን በመንግስት የሚመደቡለትን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዩንቨርሲቲው ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በጉዳዩ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባለቤት ሆነው የሚሳተፉበት የባሀል ሲምፖዚየም ለማዘጋጅት መታቀዱን ተናገረዋል።

በተግባቦቱ ላይ ጠንክሮ ከተሰራ ‘'ያንተ ያንሳል የኔ ይበልጣል'' በሚል የሚፈጠረውን ቅራኔን እንደ ሚያስቀር ጠቁመዋል።በዘርፉ በሰፊው እንዲሰራ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

አዳማ የካቲት 28 /2010 የመንግስት ከሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት