ዜና ዜና

በኢትዮጵያና ሱዳን የተጀመረው የየብስ ትራንስፖርት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ያጠናክራል - ትራንስፖርት ባለስልጣን

በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል የተጀመረው የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሁለቱን አገራት ህዝቦች ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ እንዳለው የፈዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለጸ፡፡

የፈዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኛው ከአዲስ አበባ ካርቱም የተጀመረው የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎቱ የሁለቱን አገራት ህዝቦች ትስስር ያጠናከረና ተጠቃሚነትንም ያሳደገ ነው ብለዋል፡፡

በአውሮፕላን ሲደረግ የነበረው የጉዞ ወጪ ከመቀነስ አንፃርም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አቶ ይግዛው ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል በአውሮፕላን ይጠቀም የነበረውን ተጓዥ ወጪ ከመቀነስ አንፃር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም አቶ ይግዛው ተናግረዋል፡፡

መጋቢት 2009 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካርቱም አገልግሎት መስጠት የጀመረው የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎቱ ለዘመናት የቆየውን የአገራቱ የንግድና ቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የጎላ ሚና እንዳለውም ተመልክቷል፡፡

በቀጣይም ተመሳሳይ አገልግሎት ወደ ኬንያና ጂቡቲ የመጀመር እቅድ መኖሩን ከትራንስፖርት ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመልክታል።

በሳምንት ሁለት ቀን አገልግሎቱን እየሰጠ ያለው ከአዲስ አበባ ካርቱም የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት 60 ዶለር የሚያስከፍል ሲሆን ተጓዦች ህጋዊ ፓስፖርትና ቪዛ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የካቲት 27፣2010 /ኢቢሲ/