በአማራ ክልል ቡና አብቃይ በሆኑ ወረዳዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከናወኑ ዘመናዊ የቡና ልማት ሥራዎች የተሳተፉ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታወቁ። የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ በመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ11 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን እያፈላ መሆኑን ገልጿል። በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በይነሳ ሦስቱ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ፋንታሁን ትእዛዙ እንደሚሉት፣ በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ ቡና ተክለው ማልማት ከጀመሩ አስር ዓመት ሆኗቸዋል። ይሁንና በጣዕሙና በምርቱ በገበያው ይበልጥ ተፈላጊ የሆነ ቡና ማምረት የጀመሩት ዘመናዊ የቡና ልማት ማካሄድ ከጀመሩ ወዲህ ነው።


የመንግስት ኮሙኒኬሽን ትዊት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ትዊት